Mesay Mekonnen

ህወሀት ያልፋል፡ የትግራይ ህዝብ ግን ከኢትዮጵያዊ ወገኑ ጋር ይኖራል!! (መሳይ መኮንን)

በህወሀት መዝገብ ኢትዮጵያ ለህወሀት ትኖራለች እንጂ ህወሀት ለኢትዮጵያ አይኖርም። በህወሀት መዝገብ ኢትዮጵያ የህወሀት ንብረት ናት። ኢትዮጵያ የምትኖረው የህወሀት ህልውና እስከተጠበቀ ድረስ ብቻ ነው። የህወሀቶች የአእምሮ ስሪት በዚህ አመለካከት ላይ የተዋቀረ ነው!!!

ዝም ብሎ መሞትም ያባት ነው። ህወሀቶች በመጨረሻው ሰዓትም እየለፈለፉ፡ እየቀጠፉ ይህቺን ዓለም መሰናበትን መርጠዋል። ከዚህ ሁሉ መከራ በኋላ፡ ሀገሪቱን የዓለም ጭራ አድርገው፡ ለመሰማት ጆሮን የሚያምሙ ሰብዓዊ ጥፋቶች ፈጽመው፡ ሀገር በቁም ገድለው፡ ሁለት ትውልድ አበላሽተው በመጨረሻው ሰዓት ንሰሀ ይገባሉ፡ አሟሟታቸውንም ያሳምራሉ ብለን ጠብቀን ነበር። ከሰሞኑ የህወሀት አንዳንድ መሪዎች፡ ልሂቃኖቻቸውና የፌስቡክ ሰራዊታቸው ይዘው የተነሱት ትርክት ግምታችንን ዜሮ አስገብቶታል። በራሳችን ዘመን የተፈጠረውን፡ በዓይናችን ስር የተደረገውን፡ ሰለባ የሆነው ሀገርና ህዝብ በህይወት እያለ ጻድቅ ነበርን፡ ለውለታችን ምስጋና ሲገባን ወቀሳ ምን ባጠፋን? ብለው ተነስተዋል።

ኤል ቲቪ ለህወሀቱ ጌታቸው ረዳ ያደረገውን ቃለመጠይቅ በተመለከተ ለቅምሻ ያቀበለንን አንድ ክሊፕ ተመለከትኩት። እነስብሃት ነጋ መንደር ተጠግቶ ከአዛውንቶቹ ህወሀቶች አፍ ሀሜትና አሽሙር እየሰበሰበ የሚጽፍልንን አንድ የህወሀት ቀንደኛ የፌስቡክ አዝማች ሰሞኑን የከተበውን ጽሁፍ አነበብኩት። በተለያዩ ሚዲያዎች የህወሀት ደጋፊዎች የሚሰጡትንም አስተያየትና መልዕክት አዳመጥኩት። እዚህም እዚያም በህወሀቶች ሰፈር ምን እየተባለ ነው የሚለውንም ለመቃረም ሞከርኩ። እኛና እነሱ ተለያይተናል። ከሁለት አንዳችን ተሳስተናል። ወይ እነሱ ልክ ነበሩ፡ ወይም እኛ አልተረዳናቸውም፡ አልያም የሆነ ነገር ሆነናል። ከእነስብሃት ነጋ ጋር ውስኪ እየላፈ፡ ወሬ ለቅሞ የሚነግረን አፈቀላጤያቸው ሰሞኑን የጻፈውን አንዳንድ ነገሮች ላንሳ።

”እንደ ድርጅት ከተመዘነ በሙስና ኣመለካከትና ተግባር በኣንፃራዊነት ህወሓት ከሌሎች የኢህኣዴግ ኣባልና ኣጋር ድርጅቶች የተሻለ ነው የሚል ስሜት ኣለኝ።” ይሄን መልዕክት ከማንበብዎ በፊት የልብ ድካም ችግር እንደሌብዎት እርግጠኛ ይሁኑ። ደም ግፊት፡ የሚጥል በሽታም ካለብዎት ይህን መልዕክት ባያነቡ ይመረጣል። እንግዲህ ህወሀቶች የሚያስቡት እንዲህ ነው። ለ27 ዓመታት ሀገር በአንድ ብሄር የተደራጀ የማፊያ ኢኮኖሚ መስርተው በብቸኝነት ሲግጡና ሲዘርፉ ከርመው የእነሱን ትርፍራፊና እንጥብጣቢ ኪሳቸው የወሸቁ የሌሎች ብሄር ተወላጆችን ተጠያቂ አድርገው መጥተዋልና እስኪ እንስማቸው። የጆሮ ግድግዳችን እንዳይበጠስ ብቻ እንጠንቀቅ። ህወህቶች ይናገራሉ። እንቀጥል።

” የቲም ለማ አካሄድ የኦሮሞ ሃይል ስልጣን ላይ ካልወጣ ኣገሪቱን ግጭት ውስጥ እናስገባታል: በውጤቱም ትፈረካከሳለች የሚል ነበር። ያኔ የህወሓት ኣመራር ወደ መድረክ ከመሄድ ይልቅ መላተሙን ቢያከረው ኖሮ ኣገሪቱ ወደማትወጣበት ኣዘቅትና መበታተን በገባች ነበር።” እንግዲህ ይህን የሚሉ ሀገሪቱን በ21ኛው ክፍለዘመን ባህር አልባ አድርገው፡ በከፍተኛ የሀገር ክህደት ከትውልድ ትውልድ የሚተላለፉ አያሌ ወንጀሎችን የፈጸሙት ህወህቶች ናቸው። እነሱ ለኢትዮጵያ ተቆርቁረው፡ በአንጻሩ ኢትዮጵያን ከጨለማ መንጭቀው ያወጡትንና የተስፋ ብርሃን እንድናይ ያደረጉትን የለውጥ ሃይሎች ደግሞ በሀገር አጥፊነት ፈርጀው እየከሰሱ ነው። የሚያስገርመው ይሄን የሚነግሩን ለእኛው መሆኑ ነው። በእነሱ የዘረኝነት ፖሊሲ ስቃይ መከራ ለተሸከምን ለእኛ ለኢትዮጵያውያን። እንኳን በዚህ የኢትዮጵያ

Facebook Comments

The Latest Ethiopia News

To Top