Opinion & Analysis

ዶክተር አብይ ለምን አባታቸውን ናቁ?? (by Sisay Agena)

ዶክተር አብይ ለምን አባታቸውን ናቁ??

ሴቶችን በተለይ ደግሞ እናቶቻችንን ማክበር ምንም ጠያቂ የማያሻው ትልቁ ጉዳይ ነው። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ለእናቱ ሲል አንገቱን ለካራ እንደሚሰጥ ምንም ጥርጥር የለውም!! ፖለቲከኞች ግን ሴትን ልጅ የሚያንቆለጳጵሷት ለፖለቲካ ፍጆታ ብቻ ነው።
ለምሳሌ ዶናልድ ትራምፕን ብንወሰድ ሴትን ልጅ ከመጠን በላይ እንደሚንቅ ከነጭራሹ ከልጁ ጋር ሁሉ አንሶላ መጋፈፍ እንደሚፈልግ በቪዲዮ ማስረጃ ቀርቦበታል። ስልጣን ላይ ሲወጣ ግን አይኑን በጨው ታጥቦ ሴቶችን ከማማ በላይ ሲሰቅል ተስተውሏል። በብዛት ሰልጥነናል የሚሉ ፖለቲከኞች በዓለም ላይ ያሉ ሴቶች ቁጥር በብዙ እጅ ከወንዶች ስለሚበልጥ የነሱን ድምጽ ለማግኘት ብቻ ነው ሴትን ልጅ የሚያነሷት። የሆነ ሆኖ ወደ እኛው ዶክተር አብይ ስንመጣ እናቱን በዛ መጠን ሲያደንቅ፣ሚስቱን ሲያንቆለጳጵስ፣ ጓደኞቹን መገድ እስከሚቀረው ሲያወድስ እና በቃላት ሲያሽሞነሙን…. ለምን አባቱን ስማቸውን እንኳን አልጠራም??
ፎቶዋቸውን ከዚህ ጽሁፍ በታች የምታዩት ሼህ አህመድ አሊ (የአብይ አባት)

1ኛ/ ሙስሊም ናቸው

2ኛ/ የኦፌኮ አባል ናቸው

ዶክተር አብይ ህጻን የሰባት ዓመት ከስድስት ወር ልጅ እያለ እናቱ በሞት ሲለዩት (ነብሳቸውን በገነት ያኑረው) እንደ እናትም እንደ አባትም ሆነው ያሳደጉት ሼህ አህመድ አሊ ናቸው። እንደሚወራው ከሆነ በጣም በችግር ውስጥ ነው የሚኖሩት። ከዚህ ቀደም ለቤት ክራይ የሚከፍሉት አጥተው እንዲረዳቸው ሽማግሌ አስልከው ቢጠይቁትም ቃል በቃል “ጌታን ከተቀበለ፤ ጴንጤ ከሆነ ሁሉንም ነገር አደርግለታለው ፤ ካልሆነ ግን ለአህዛብ(ሙስሊምን ነው እህዛብ ብለው የሚጠሩት) ምንም እርዳታ አላደርግም!!” ብሎ አባቱን ክዷል።
እንደዛሬው ኦህዴድ ጥርስ ሳያወጣ ለህወሃት ታማኝ ባሪያ በነበረበት ዘመን ከብዙ የኦፌኮ አባላቶች ጋር አባቱንም እንዲታሰሩ አድርጓል።
አባቱ አሁን አጋሮ በሚገኘው የኦፌኮ ጽህፈት ቤት ውስጥ በጥበቃ ነው የሚተዳደሩት።
ዶክተር አብይ ለእስልምና ከበፊትም ጥላቻ ስለነበረው ምእራባውያን እሱ የኢትዮጵያ መሪ እንዲሆን ህወሃትን አንቀው ይዘው ነበር። እንደሚታወቀው ባራክ ሁሴን ኦባማ በአባታቸው ሙስሊም ነበሩ ግን እስልምናን አምርረው ይጠላሉ። እነሱም በየትኛውም ሚዲያ ስለአባታቸው አንስተው አያውቁም ። ሁሌ ሲያነሱ የነበሩት ስለ ነጭ ክርስቲያን እናታቸው እና አያታቸው ብቻ ነው።
አብይም በአርባ ደቂቃ ንግግር ውስጥ እንዴ እንኳን የአባታቸውን ስም ሳያነሱ ለአባታቸው ያላቸውን ንቀት ፍንትው አድርገው አሳይተዋል።
የህወሃት ባሪያ መሆንም፤ የምእራባውያን ባሪያ መሆንም ለአንዲት ሃገራችን ኢትዮጵያ ጥቅም የለውም!!
ሰውን በሃይማኖቱ መጥላት አግባብ አይደለም፤ በተለይ አባትን የሚያክል ንጉስ.. ሙስሊም ስለሆነና የተቃዋሚ ፓርቲ አባል ስለሆነ ከታሪክ ማህደር ላይ መፋቅ ወንጀል ነው!!!
ማጠቃለያ:- ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ አባቱን የእስልምና እምነት ተከታይ እና የኦፌኮ ፓርቲ አባል በመሆናቸው ብቻ በተደጋጋሚ ስቃይ ያደርስባቸው ነበር። ይሄንንም በትላንት መግለጫው ስማቸውን ለአንዴ እንኳን ባለማንሳት ጥላቻውን በግልጽ አሳይቷል።
ኢትዮጵያ ሁሉም ሃይማኖት በእኩልነት የሚኖርባትን ስርአት የሚቀርጽ መሪ ትሻለች!!

Share
error0

Facebook Comments

The Latest Ethiopia News

To Top