Ethiopia Breaking News

የኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ጠቅላይ ሚኒስትሩን እየጠበቀ መሆኑን አስታወቀ

የኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት በኢሊሊ ሆቴል ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫው ጠቅላይ ሚንስትራችን ቃል መሰረት በቅርቡ ተገናኝተን በመፍትሄዎቹ ላይ ለመነጋገር እየጠበቅን ነው አለ::

ሙሉ መግለጫው ለዘ-ሐበሻ ደርሷል እንደሚከተለው ይቀርባል::

ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በ8/10/2010 የኢድ አልፊጥር በአልን ምክንያት በማድረግ ባስተላለፉት መልዕክት ላይ የህዝበ ሙስሊሙን ያልተመለሱ ጥያቄዎች ለመመለስ ዝግጁ መሆናቸውን በመግለፅ ጥሪ አድርገዋል።

እኛ የሙስሊሙ ህብረተሰብ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ግልፅ የሆነ ደብዳቤያችንን ለጠቅላይ ሚንስትሩ በፅህፈት ቤታቸው በኩል አስገብተናል።

በክቡር ጠቅላይ ሚንስትራችን ቃል መሰረት በቅርቡ ተገናኝተን በመፍትሄዎቹ ላይ ለመነጋገር እየጠበቅን ሲሆን በዚህ ጋዜጣዊ መግለጫችን ላይ የተወሰኑ ነጥቦችን ለህዝባችን እና ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ግልፅ ለማድረግ እንፈልጋለን።

1. ህዝበ ሙስሊሙ የጣለብንን መፍትሄ የማፈላለግ ሃላፊነታችንን ለመወጣት ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ማዕከል ያደረገ፣አካታች የመፍትሄ አቅጣጫ እንከተላለን።ለዚህም ዑለሞችን ፣ምሁራንን፣የሀገር ሽማግሌዎችን፣ወጣቶችና ሴቶችን እንዲሳተፋ እናደርጋለን። እንዲሁም የህዝበ ሙስሊሙን ጥቅም የሚያስጠብቅና የተሻለ መፍትሄዎች ያላቸው ግለሰቦች፣ ተቋማትና ምሁራን የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱና አብረውን እንዲሰሩ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ።

2)የምንፈልገው መፍትሄ አሳታፊ ፣ ዘላቂና ሁለንተናዊ የህዝበ ሙስሊሙ መብት የሚከበርበት መሆን ስላለበት ህዝባችን ይህንን ተገንዝቦ በአንድነት መንፈስና በትዕግስት ከጎናችን በመቆም በላቀ ትብብር አብረን እንድንዘልቅ አደራችን የጠበቀ ነው።

3)በሃገራችን ባለፉት ሁለት ወራት እየሆነ ያለውን ይበል የሚያሰኝ ለውጥ ያስተዋለውንና ያነሳቸው የመብት ጥያቄዎች አፋጣኝና አርኪ ምላሽ ያገኙ ዘንድ በጉጉት የሚጠብቀውን ህዝባችንን በአፍራሽና ተስፋ በሚያስቆርጥ ወከባ ሊጠቀሙበት የሚፈልጉትን ለዚህም ያደቡትን አካላባገለለ እንደማይላቸው ከማወቃችንም ጋር ህዝባችን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት ልናሳስብ እንወዳለን።

4) ሀገራችንን ያስተዳደሩ መንግስታት በሙሉ ሙስሊሙን ባገለለ ፖሊሲያቸው ተመሳሳይ አቋም ያራምዱ የነበረ ሲሆን በህገ መንግስትና በፖሊሲ ደረጃ በኢህአዲግ መንግስት መልካም ጅማሮዎች እንደነበሩ አይካድም።በአፈፃፀም ደረጃ ግን በሙስሊሙ ላይ ተመሳሳይ በደሎች ፈፅሞል።ሆኖም ህዝብ ለህዝብ የነበረን ታሪካዊና አኩሪ አብሮ የመኖር ባህላችን በዚህ ዘመን ከተደገሰልን አጥፊ እቅድ ታድጎናል። በመሆኑም ህዝባችን ይህንኑ አኩሪ ባህል አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪያችንን እናቀርባለን።

5) በአገር ውስጥና በውጭ አገር የምትገኙ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን በሙሉ እንደተለመደው በምትችሉት ሁሉ እገዛችሁና አብሮነታችሁ እንደማይለየን በፅኑ እናምናለን።

6) የምንፈልገው መፍትሄ አሳታፊ ፣ ዘላቂና ሁለንተናዊ የህዝበ ሙስሊሙ መብት የሚከበርበት መሆን ስላለበት ህዝባችንን ይህንን ተገንዝቦ በአንድነት መንፈስና በትዕግስት ከጎናችን በመቆም በላቀ ትብብር አብረን እንድንዘልቅ አደራ የጠበቀ ነው።

Share
error0

Facebook Comments

The Latest Ethiopia News

To Top