Ethiopia Breaking News

ዶ/ር መረራ ጉዲና በወሊሶ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና በወሊሶ ከተማ ደማቅ የክብር አቀባበል ተደረገላቸው:: የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን መነሳት ተከትሎ በወሊሶ ስታዲየም ውስጥ በዛሬው ዕለት በተደረገው ሕዝባዊ ስብሰባ ቄሮን እና የወሊሶን ሕዝብ አመስግነው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለህዝቡ ንግግር አድርገዋል::

ነዋሪነቱን ወሊሶ ያደረገው መምህር ስዩም ተሾመ ለዶ/ር መረራ ጉዲና የተደረገውን አቀባበል በተመለከተ ሲገልጽ “ይህ ወሊሶ ነው! ወሊሶ የገረሱ ዱኪ ሀገር ነው! ባርነትና ጭቆናን የሚጠየፉ ጀግኖች የተወለዱበት፣ ፋሽስት ኢጣሊያንን ተዋግተው ያሸነፉ አርበኞች እትብት የተቀበረበት ነው፡፡ የነፃነት ታጋይ ወደ ወሊሶ ሲመጣ ጀግናቸውን ይዘክራሉ፣ የገረሱን አረዓያ እንዲከተል ምስሉን የክብር ስጦታ አድርገው ያበረክታሉ!!! የቀድሞ አርበኞችን እየዘከሩ ለነፃነትና እኩልነት ለሚታገሉ ክብርና ምስጋና ያቀርባሉ!!! ምክኒያቱም ይሄ ወሊሶ ነው! ጭቆናን የሚጠየፉ ጀግኖች የሚወለዱበት፣ ለዝንተ-ዓለም የሚዘከሩበት ሀገር ነው!!!:” ብሎታል::

ዶ/ር መረራ ጉዲና እና በቅርብ ከ እስር የተፈቱ የ ኦፌኮ አመራሮች በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ሕዝባዊ ስብሰባዎችን በተከታታይ እንደሚያደርጉ ከወጣው መርሃ ግብር ለመረዳት ተችሏል:: ኦፌኮ ራሱን ይበልጥ በማደራጀት ባለፉት 4 ወራት ብቻ ከ5 የሚበልጡ ጽህፈት ቤቶችን በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ከፍቷል::

Share
error0

Facebook Comments

The Latest Ethiopia News

To Top