Ethiopia Breaking News

ዶ/ር ዓብይ አህመድ ትናንት ከስልጣኑ የተነሳውን የደህነንት ሚ/ር ጌታቸው አሰፋ የጠቅላይ ሚኒስተሩ የደህንነት አማካሪ አድርገው በመሾም ስህተት እንዳይሰሩ ተመከረ

በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያው ሊባል በሚችል መልኩ በትናንትናው ዕለት ሃገሪቱ አምስት ሰበር ዜናዎችን አስተናግዳለች:: የሳሞራ የኑስ መነሳት:: በቅርቡ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪነት የተሾሙት አባዱላ ገመዳና ጠቅላይ ሚ/ሩን በአሜሪካ ጉዳዮች የሚያማክሩት አምባሳደር ግርማ ብሩ መሰናበት; የጌታቸው አሰፋ መነሳትና የነጀነራል አለምሸት ደግፌና ጀነራል አሳምነው ጽጌ ሙሉ ማዕረግ ተመልሶ በክብር ጡረታ እንዲወጡ መደረጉ እንዲሁም ጀነራል ሰዓረ መኮንን ኢታማዦር ሹም ሆኖ መሾሙ::

በተለይ ለብዙ ንጹሃን ደም ተጠያቂ ነው የሚባለው የደህንነቱ ሹም አቶ ጌታቸው አሰፋ መነሳቱ ብዙዎችን ያስገረመ ሲሆን መነጋገሪያ መሆኑም አልቀረም:: በአልጀዚራ ላይ ትንታኔዎችን የሚያቀርበው መሐመድ አደሞ ጌታቸው አሰፋን በተኩት በአዲሱ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ጄኔራል አደም መሐመድ ሹመት ዙሪያ አስተያየቱን ሲሰጥ “ላለፉት 17 ዓመታት ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሃገሪቱ የደህንነት ዳይሬክተር ጌታቸው አሰፋ ማን እንደሆነ በመልክም በአካልም የሚያውቀው የለም:: ለሕዝብ የቀረበ ፎቶ የለም:: አሁን ግን በፎቶ የምናውቀው ጄኔራል አደም መሐመድ መሾሙ ጥሩ ነው:: ይህ የዶ/ር ዓብይን የግልጽነት አመራር ያሳያል” ብሎታል::

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በበኩሉ ጌታቸው አሰፋ መነሳቱን ደግፉ ሆኖም ግን ትናንት ከስጣናቸው የተነሱትን የአባዱላ ገመዳን ቦታ ተክቶ ጌታቸው አሰፋ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ ሆኖ እንዳይመጣ ስጋት አለው:: “ጌታቸው አሰፋ ትላንት ጡረታ በወጣው አባዱላ ገመዳ ቦታ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ ተደርጎ እንዳይሾም አጥብቄ እመክራለሁ። ጅምሩን ሊያደናቅፈው ይችላልና።” ብሏል::

የተመስገንን ሙሉ መረጃ በሌቭዲዮ በጤናዳም ዩቱብ ቻናል — Click Here

ሌሎች በርካታ አክቲቭስቶችም ዶ/ር ዓብይ የደህነንት ሚ/ር ጌታቸው አሰፋ የጠቅላይ ሚኒስተሩ የደህንነት አማካሪ አድርገው በመሾም ስህተት እንዳይሰሩ እየመከሩ ይገኛሉ::

Share
error0

Facebook Comments

The Latest Ethiopia News

To Top