Ethiopia Breaking News

የዋልድባ መነኮሳት እጃቸውን በካቴና ታስረው ፍርድ ቤት እንደመጡት በካቴና ታስረው ወደ ቂሊንጦ እስር ቤት ተመልሰዋል

የዋልድባ መነኮሳት እጃቸውን በካቴና ታስረው ፍርድ ቤት እንደመጡት በካቴና ታስረው ወደ ቂሊንጦ እስር ቤት ተመልሰዋል

ሰለሞን ቦጋለ 

አባቶቻችን ዛሬም ለመጋቢት 18 ተቀጥረዋል፣ በካቴናም ታስረው ወደ ቂሊንጦም ተመልሰዋል

በቂልንጦ እስር ቤት የሚገኙ የዋልድባ መነኮሳት ወደ “ፍርድ ቤት” ሲሄዱ – መጋቢት 11 2010 ዓ.ም

~ አክሱማዊ ነኝ ባዩዋ #ህወሓት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶን ለመበቀል ፣ አከርካሪዋንም ለመስበር እሠራለሁ ባለችው መሰረት እነሆ ዛሬም አባቶቻችንን #በሰንሰለት አስራ በአደባባይ በማንከራተት ተሳልቃባቸዋለች። በሰፈሩት ቁና አለ ሌኒን ። [ #ህወሓት_ሆይ_ይመችሽ ]

#ETHIOPIA | ~ አዲስአበባ ~ ቂሊንጦ ~ ዋልድባ

የዛሬው ችሎት ከወትሮው እጅጉን ዘግይቶ የተሰየመ ሲሆን ዓቃቤ ህጉም ያለመገኘቱ ተነግሯል ። በችሎቱም ላይ የታየው የህዝቡ ቁጥር ግን እጅግ አስደንጋጭና በጣም ደስስስ ይልም ነበር ተብሏል ። የፍትህ አዳራሹ ሞልቶ ሰዉ ከችሎቱ ውጭ ፈስሶ ይታይ ነበርም ተብሏል ።

~ በዛሬው ችሎት የአባቶች ጠበቃ የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የታሰሩትን እስረኞች አያያዝ እንዳሻሻለና አባ ገብረኢየሱስን ከዞን 5 ጭለማ ቤት ፣ አባ ገብረሥላሴን ከዞን 3 በመቀየር ሁለቱንም በአንድ ላይ በዞን 1 እንዲታሰሩ ማድረጉንና እስከዛሬ የከለከለውንም የመነኮሳቱን አልባሳት እንዲገባላቸው መፍቀዱን ጠቅሰው ለፍርድ በቱ አሳውቀዋል።

ፍርድ ቤቱም መጋቢት 18/2010 ዓም የዓቃቤ ህግን የምስክሮችን ቃል ለመስማት ቀጠሮ በመያዝ የአባቶችን ክስ እንዳይቋረጥና እንዲቀጥል በማድረግ የዕለቱን ችሎት አጠናቅቋል ።

ዛሬ በአባቶቻችን ገጽታ ላይ እጅግ ደስ የሚል ብሩህ የሆነ ፈገግታና የተረጋጋ ስሜት ይታይ እንደነበር የመረጃ ምንጮቼ ገልጸውልኛል። እጆቻቸው በካቴና መታሰሩ እንደቀጠለ ሲሆን ይኽ አገዛዙ ለተመልካቾች ምን ያኽል ” የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ለማዋረድ ቆርጦ መነሳቱን የሚያሳይ ነውም ተብሏል የታሠርም አይመሥል ። ከነጸጋቸው ደስ ይሉ ነበረም ብለዋል የመረጃ ምንጮቼ ፡፡

~ በሌላ በኩል በዛሬው ዕለት ከወትሮው በተለየ መልኩ ቁጥሩ እጅግ በዛ ያለ ህዝብ መገኘቱ ሌላው የፍርድቤት ሠራተኞችን ጭምር ያስደሰተ እንደነበር በዚያው በልደታ ፍርድ ቤት ውስጥ የሚሠሩ የመረጃ ምንጮቼ ገልጸውልኛል። ነገር ግን የአባቶችን ችሎት ለመከታተል የአዲስ አበባ ምእመናን ቸልተኝነት ማሳየታቸው እየተወቀሰም ይገኛል ።

~ ለበዓለ ጥምቀት ምንጣፍ ማንጠፍ ብቻውን ክርስቲያን አያስብልም ። ገንዘብ የሚገኝበት ቦታ ብቻ አለሁ አለሁ ማለት ፣ ከበሮ እየመቱ መዘመር ብቻ ባለበት ቦታ መገኘት ሳይሆን በእንደዚህ አይነቱ ቦታም በመገኘት ከአባቶቻችን ጎን መቆሙ በራሱ በረከት ከማሰጠቱም አልፎ ለአሳሪዎች ከበድ ያለ መልእክት ማስተላለፊያ መንገድም ጭምር ነው።

~ ዛሬም ከሲኖዶሱ አባቶች በፍርድ ቤቱ አካባቢ የተገኙ ባይኖርም በእዚሁ በፌስቡክ የሚለቀቀውን መረጃ በመስማት ከምእመናን ባሻገርም እንደተለመደው የብስራተ ገብርኤሉ አረጋዊው አባ ተበጀ ችሎቱን ለመከታተል በስፍራው ተገኝተው ታይተዋል ። በተለይ እናቶቻችን ሊመሰገኑ ይገባል ። ወጣቶችም እንዲሁ ልትመሰገኑ ይገባል ። ባለፈው ሰኞ አንዲት በክራንች የምትሔድ እህት ችሎቱን ለመከታተልና በዚያውም ከአባቶቻችን በረከት ለመቀበል የመጣች ሲሆን በዛሬው ዕለትም አንዲት በክራንች የምትሔድ እህት በችሎቱ ታድማ ታይታለች ።

በቂልንጦ እስር ቤት የሚገኙ የዋልድባ መነኮሳት ወደ “የፍርድ ቤት” ውሎ ለመከታተህ ፍርድ ቤት የተሰባሰበው ህዝብ – መጋቢት 11 2010 ዓ.ም

~ ለእኔ ለዘመዴ ፎቶ እያነሱ ይሰጡ ይሆናል ተብለው የተጠረጠሩ ሰዎች ስልካቸው ለጊዜው የታገተ ቢሆንም ለእኔ ከሚላከው ፎቶ ጋር የሚመሳሰል ሆኖ ባለመገኘቱ እየተገሰፁ ተለቀዋልም ተብሏል ።

~ እንደተለመደው ማኅበራትና ምእመናን ቅዳሜና እሁድ ቂሊንጦ ሔዳችሁ ከአባቶቻችሁ በረከት ተቀበሉ ። የፊታችን መጋቢት 18/2010ም ፍርድ ቤት በመምጣት ከአባቶቻችን ጎን በመቆም ለሃይማኖታችሁ ያላችሁን ታማኝነት እንድታስመስክሩ ይሁን ።

ቸር ወሬ ያሰማን ።

~ድልና ትንሣኤ ለኢትዮጵያ ሀገሬና ለተዋሕዶ ሃይማኖታችን.! ውድቀትና ጥፋት ፤ ለሁለቱም ጠላቶች። አራት ነጥብ ።

እነሆ ለዛሬ አበቃሁ.! ነገርግን እግዚአብሔር ቢፈቅድ ነገ ደግሞ እቀጥላለሁ ።

” እኔ ግን እላለሁ !!! እምዬ ኦርቶዶክስ አንቺ እናት ዓለም ፤ የእነ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ፣ የእነ ቅዱስ አትናቴዎስ እና ቅዱስ ቄርሎስ የእነ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ የእነ ቅድስት አርሴማ ፣ የእነ አቡነ ተክለሃይማኖት ፣ የእነ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ፣ የአባ ሳሙኤል ዘዋልድባና የአቡነ አረጋዊ ሃይማኖታቸው የሆንሽ ንጽህት ተዋሕዶ ሃይማኖቴ ሆይ ! ብረሳሽና ብከዳሽ ቀኜም ትርሳኝ፣ ትክዳኝም ። ባላስብሽና ባልሞትልሽ ምላሴ ከጉሮሮዬ ይጣበቅ ። ሳለጎበድድና ሳለከዳሽ እንድኖር አምላክሽ ይርዳኝ ። ይህን ባለደርግና ሳልጮህልሽ ዝም ብዬ ብሞት ስሜ ከህይወት መጽሐፍ ይደምሰስ ።

“ጌታ ሆይ! ከዚህ በፊት በሆነው ፤ አሁንም እየሆነ ባለው እና ወደፊትም በሚሆነው ነገር ፤ ክብሩን ሁሉ አንተ ውሰድ አሜን. !

“ድንግል ሆይ እናቴ ! አዛኝቱ ዛሬም እንደትናንቱ ቅደሚ ከፊት ከኋላዬ”

Share
error0

Facebook Comments

The Latest Ethiopia News

To Top