Amharic

የለማ መገርሳ አስተዳደር የክልሉን ሰላም ለማረጋገጥ ልዩ ትኩረት በመስጠት እንደሚሰራ ገለፀ

በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች መንግስት የዜጎችን ደህንነት እንዲያስጠብቅ የሚጠይቁ ሰልፎች እየተካሄዱ ባለበት ወቅት የኦሮሚያ ክልል ካቢኔ 4ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዶ በወቅታዊ ሁኔታዎች ጉዳይ በመወያየት ውሳኔ ማሳለፉን የአቶ ለማ አስተዳደር አስታወቀ::

የክልሉ ካቢኒኤ ባካሄደው 4ኛ መደበኛ ስብሰባው የክልሉ መንግስት ካቢኔ በሰላም ጉዳይ ላይ ትኩረት ሰጥቶ የተወያየ ሲሆን፥ በተለይም በምእራብ ኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ላይ ባጋጠመው የፀጥታ ችግር ዙሪያ ተነጋግሮ በዚህም ያጋጠመውን የፀጥታ ችግር ተከትሎ እየደረሰ ያለው የሰው ህይወት መጥፋት እና የዜጎች መፈናቀል እንዲቆም ብሄራዊ የደህንነት ምክር ቤት ያሳለፈውን ውሳኔ ሙሉ በሙሉ እንደሚደግፍ እና ስራ ላይ እንዲውል እንደሚሰራ ይፋ አድርጓል::

የክልሉ ህዝብ የህግ የበላይነት እንዲከበር እና የሀገሪቱ ሰላም እንዲሰፍን እያቀረበ ባለው ጥያቄ መሰረትም እርምጃዎች መውሰድ መጀመራቸውን እና ይህም ተጠናክሮ የሚቀጠል መሆኑን የገለጸው የአቶ ለማ ካቢኔ እስካሁን በተወሰደው እርምጃም በዜጎች ላይ አሰቃቂ ወንጀል የፈፀሙ ከ200 በላይ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን እና የተቀሩትንም በቁጥጥር ስር በማዋል ለህግ የማቅረብ ስራ እንደሚሰራ ገልጿል::

የሰላም ጉዳይ ከሁሉም ጉዳይ በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው በመሆኑ በግጭቱ ምክንያት ችግር ያጋጠማቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ለመርዳት ሰፋፊ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም የለማ አስተዳደር ጠቅሶ ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚደረገው ድጋፍም ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና በዜጎች ላይ እየተፈፀመ ያለው ግድያ እንዲቆም እና ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ለሚሰሩ የፀጥታ ሀይሎች ድጋፍ እንደሚደረግም ነው ገልጿል::

የአቶ ለማ ካቢኔ ችግሩን ከምንጩ ለመቅረፍ እየተከናወነ ባለው ስራ ውስጥ ህብረተሰቡ ለጥፋት ሀይሎች በር ለመክፈት የሚጥሩትን በንቃት እንዲጠብቅ እና እንዲከላከለም ጥሪ አቅርቧል::

ይህ በ እንዲህ እንዳለ «ተጠላልፎ ከመዉደቅ ተደጋግፎ መራመድ» በሚል መሪ ቃል የኦሮሞ ዴሞክራስያዊ ፓርቲ /ኦዴፓ/በኦሮሞና በኦሮሚያ ጉዳዮች ላይ የሚሰሩ ከ10 በላይ ተፎካካር የፖለቲካ ፓርቲዎችጋር ሰሞኑን እንደሚወያይ የፓርቲዉ የኮሙኒኬሼን ጉዳዮች አቶ ታዬ ደንደአ ገለጹ::

ኦዴፓ አንድ ጠንካራ ፓርቲን ለመመስረት ዕቅዳቸዉ፣ ፕሮግራማቸዉ እና ስልታቸው ከሚመሳሰል ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር እየተወያየ እንደሚገኝም የፓርቲው የኮሙኒኬሼን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ታዬ ደንደአ የገለጹ ሲሆን በኦቦ ዳዉድ ኢብሳ የሚመራው የኦሮሞ ነፃነት ግንባርን /ኦነግ/፣ በጀኔራል ከማል ገልቹ የሚመራዉ አንድነት ኦነግን ጨምሮ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር ኦዴፓ እየተወያዩ እንደሚገኝም ጠቁመዋል::

አጀንዳቸዉ ከኦዴፓ ጋር የሚመሳሰል ጋር አንድ በመሆን፣ አጅንዳቸዉ ከኛ ጋር ከማይመሳሰለው ጋር ደግሞ ሕዝብን ወደፊት በሚያሻግሩ ጉዳዮች ላይ መረዳዳት ሊኖር ይገባል» የሚለው የፓርቲያቸዉ አቋም እንደሆነም አቶ ታዬ ከዲደብሊው ጋር ባደረጉት አጭር ቆይታ ገልፀዋል።

Share
error0

Facebook Comments

The Latest Ethiopia News

To Top