Amharic

ኢትዮጵያዊው ፒላጦስ በርከት ስምኦን

የተስፋ ልጅ

በጣም በሚገርም እና በሚያስገርም ሁኔታ አቶ በረከት ሁለተኛ መፅሀፋቸውን ለአንባብያን አብቅተዋል እጅግ የሚገርመው መፅሀፍ መፃፋቸው ሳይሆን መፅሀፋን ለምን እንዴት እንደፃፋት የገለፁበት መንገድ ነው።

በኢትዮጵያውያን ላይ ለደረሰው እልቂት እስር እንግልት ሞት ስደት በተለይም በ1997 ምርጫ ወቅት በአዲስ አበባው የህዝብ እልቂት ዋነኛው ተጠያቂ የሆኑት አቶ በረከት ስምኦን እንደ ፒላጦስ እጃቸውን በመታጠብ ሰው እንዲገደል እንዲሰደድ እንዲታሰር በፈረሙበት እጃቸው ትንሳኤ ዘ ኢትዮጵያ በሚል እርስ መፅሐፋ ፅፈው ስለ መፅሀፋችው ይህንን አሉ።

የፃፍኩት ዛሬን ብቻ እያሰቡ ህይወታቸውን ያለ ትህትና ለሚኖሩና ለሚመሩ ሰዎች የፍርድ ቀን በሰማይ ቤት ብቻ ሳይሆን በምድርም ላይ እንዳለ ለማሳየት ነው በማለት ለህዝብ ያላቸውን ንቀት በአደባባይ ለንባብ እንዲበቃ መፅሀፍ ፅፈው አቅርበዋል!!!

እጅግ በጣም ያሳፍራል እጅግም ለህብረተሰቡ ያላቸውን ንቀት ያሳዩበት መፅሀፍ ነው ሁለተኛው ነጥብ ደግሞ ምን ይላል

” ከቅርብ ግዜ ወዲህ ደግሞ በፌዴራል እና በሁሉም ክልሎች የምታዘበውን የማን አለብኝነት አዝማሚያ በግልፅ በአደባባይ በመግጠም በትንቢት ለተሞሉ መሪዎች የዲሞክራሲያችን ወርድ እና ስፋት ለማሳየት እና የምንወስናቸው ውሳኔዎች ኃላፊነትና ተጠያቂነት እንደማይቀርልን ለማስገንዘብ ነው”

እረ ጎበዝ እንዴት ነው ነገሩ ቆይ ይህ ህዝብ ማን ምን እንደሚያደርግ ማን ምን አይነት ወንጀል እንደሰራ ማን ማን አለብኝ ብሎ የመንግስትን ስልጣን እንደሚዘውር አያውቅም ብሎ አስቦ ነው እንዴ አቶ በረከት ይህንን ነጥብ ያነሳው በሚገርም ሁኔታ እሱ ነው በትእቢቱ ተወጥሮ ሀገሪቱን ከማትወጣበት አዘቅት የከተታት እሱ ነው በማያገባው ጉዳይ በክልሎች እየገባ ውሳኔ የሚያስልለብስ እንዴት ሆኖ ነው እሱ ሳይጠየቅ ተጠያቂነትን የሚያስገነዝበን።

ሶስተኛው ነጥብ ደግሞ ታላቁ የግሪክ ፋላስፋ ፕሉቶ እንዳለው ” የምጨነቀው ለአሁኑ ሳይሆን ከስድስት መቶ አመት በኃላ ለኖረው ስሜ ነው እንዳለው ብለው ይቀጥላሉ።

እንኳን አቶ በረከት ስምኦን መለስ ዜናዊም በስድስት አመት ተረስቷል ህዝቡ ግን ምንም አያገናዝብም ሁሌም የምንጭንበትን ይቀበላል ብለው አስበው ከሆነ ተሳስተዋል በህዝብ ዘንድ እንኳን ከስድስት መቶ አመት በኃላ በሞቱ ከስድስት ወር በኃላም የሚያስታውሳቸው አይኖርም ምክንያቱም በህዝቡ ላይ ያደረሱት በደል የሚያቀባብር አይደለም የሚያስተዛዝን ሀውልት የሚያስቆም ስራ አይደለም የሚያሰቅል ወንጀል ነው በ27 ግዜ ውስጥ የፈፀመው በረከት ስምኦን።

 

በመጨረሻም እጅግ እጅግ ያሳዘነኝ ነገር የዚችኛዋ ነጠብ ነገር ነች ምን ይላሉ አቶ በረከት አንዱ መፅሀፉን ለምን እንደፃፋት ሲያብራሩ፦

“የፍርድ ቀንን ከሰማይ ሲጠብቁ ጊዜ ያላቸው የሚመስላቸው ሁሉ ማህበራዊ ብይን እዚሁ በምድር ላይ ከቅርባቸው እንደሚያገኙት ለማሳየትም ጭምር ነው”

ይህኛው ጨርቅ አስጥሎ ያስሮጣል በአደባባይ የገዛ ጓዳቸውን የሚያሳስሩ ለምሳሌ ታምራት ላይኔን መላኩ ፋንታን ልብ ይሏል የአዲስ አበባን ህዝብ በአጋዚ ያስጨፈጨፋ የአማራውን ህዝብ የህውሀት ሎሌ ያደረጉ እጅግ ብዙ የንፁህ ነብሶች በእጃቸው ላይ ያለች ሰው እንደ ፒላጦስ እጃቸውን ታጥበው “የፍርድ ቀንን ከሰማይ ሲጠብቁ ጊዜ ያላቸው የሚመስላቸው ሁሉ ማህበራዊ ብይን እዚሁ በምድር ላይ ከቅርባቸው እንደሚያገኙት ለማሳየትም ጭምር ነው” ሲሉ ሀበስ ገበርኩ ያስብላል።

ከመጨረሻው ገፅ የተወሰደ

Share
error0

Facebook Comments

The Latest Ethiopia News

To Top