Amharic

ዶ/ር አብይ አህመድ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሚዲያ ባለሙያዎች ጋር ሊወያዩ ነው

ወደ ስልጣን ከወጡ ጀምሮ ከማንኛውም ጋዜጠኛ ጋር ቃለምልልስ አድርገው የማያውቁት ዶ/ር አብይ አህመድ ከሚዲያ ሰዎች ጋር በቀጣዮቹ ሁለት ወይም ሦስት ቀናት ውስጥ እንደሚገናኙ ታወቀ::

የመንግሰት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ ይህንን አረጋግጠዋል:: ዶ/ር አብይ አህመድ እስካሁን ለሕዝብ የሚቀርቡ ቭዲዮዎቻቸው ተቀርጸው ለሕዝብ የሚደርሱና ከስብሰባዎች ላይ የተቀረጹ ሲሆን ከጋዜጠኞች ጋር ቁጭ ብለው ፕሬስ ኮንፈረንስ ሰጥተው አያውቁም::

በዋሽንግተን ዲሲ ለጉብኝት በመጡበት ወቅትም በተለይ በውጭ ሃገር የሚገኙ ጋዜጠኞች ከጠቅላይ ሚኒስተሩ ጋር ቃለምልልስና ውይይቶችን ለማድረግ ጥያቄዎችን አቅርበው የነበረ ቢሆንም ሳይሳካ ቀርቷል::

Share
error0

Facebook Comments

The Latest Ethiopia News

To Top