Amharic

በመላው ሀገራችንና በተለይ በቅርብጊዜ ከወልድያና ቆቦ ትርምስ በስተጀርባ ያለው ማነው? (ከአስገደ ገብረስላሴ )

በኣሁኑ ጊዜ በሀገራችን ያለው ጭቆና ፣ስራ ኣጥነት ፣ስደት የውሼት ልማት ምክንያት  ብሶት  የወለደው ምክንያት በተከመረ ገለባ በመፈጠሩ  የእሳት ሰደድ በኣንዱ ኣቅጣጫ  ሲጠፋ  እንደገና በሌላ ኣቅጣጫ  እየተቀጣጠለ እየተባባሰ  የቡዙ ወገናኖች እልቂት  እና የሀብት  ውድመት ጠንቅ ሆኖዋል ።

ኣስገደ ገብረስላሴ

 

 

 

 

 

 

 

 

ይሀ የወጣቶች የተቃውሞ የእሳት ሰደድ ጠንቁና ወደ ኣውዳምነት  የነዳው ማነው  ለሚለው ጥያቄ ?  መቋጫውስ የት ነው ? ለሚለው ግን መልሱ ?
1 .   የኢህኣደግ የከፋ  ዲሞክራሲያዊ ፡ኣፈና፣የተባላሸ ፓለቲካዊ ኣስተሳሰብ ( ኣይዶሎጂ )፡ የወደቀ ኢኮኖሚያዊ  ፓሊሲ የወለደው  መራራ ድህነት እና ስራ ኣጥነት  በመኖሩ !!!!
2.  የሀገራችን ሀብት በኢህኣደግ ባለስልጣናት ከነመዋቅራቸው እና ሸሪኮቻቸው ጥቂት ባለሀብቶች  ተወሮ በሞኖፓል በመያዙ ህዝቡ ሰለደኸዬ ።
3 . በሁሉም የሀገራችን ከተሞች  ኣካባቢ  የሚገኙ የኣርሶ ኣደሩ መሬት ኣብዛኞቹ ያለመሬት ግምት ተወረው ጥቂቶቹም በኣንስተኛ ግምት ተወረው በውድ ዋጋ ተሸጠው ለባለስልጣናት እና ሸሪኮቻቸው  ለጆቻቸው የሀብት መካበቻ ፣ለቅንጦትበመዋላቸው  ህዝቡ የእለት ጉርስም  በሀገሩ መኖር ስላልቻለየህዝብ ብሶት በመስፋቱ ።
4  ፡ በቋንቋና በባህል  ብቻ የተካለለው  የፈደራሊዝም ኣወቃቀር  ያቃጣጠለው እሳት ።

5 . በሀገራችን ያሉ  የኢህኣደግ ተወዳዳሪ ፓለቲካ ፓርቲዎች  ተባብረው እና ኣንድነት ፈጥረው የህዝብ ጥያቄ  ኣስተባብረው ሳይንሳዊ ኣማራር እንደመስጠት ፈንታ ፡ጥቂት የማይባሉ በኢህኣደግ መሪዎች  በህዝብ ስም  የሚነግዱበት  የንግድ እና የእንድስትሪ ድርጅቶች ሀብት  በጥቅም እየተገዙ ኣገራቸውና ህዝባቸው የካዱ በስመ  ህገመንግስት  ማሰተካከያ ድርድር እየቀለዱ  በዜጎች የሚጫወቱ ። የቀሩ ደግሞ ምንም የሀሳብ ልዩነት የሌላቸው ገና ለገና ለስልጣን የሚሮሯሯጡ ወደ ህዝብ ወርደው ኣማራር የማይሰጡ ፣በመግለጫ ብቻ በኣዬር የተንሳፈፉ  ኢህኣደግ በፈጠረው ቡሶት የተፈጠረው የእሳት ሰደድ  ለማጥፋት ኣማራር ። እንደመስጠት ፈንታ   በገን ሆነው በመመልከታቸው  ጭቁኖች  በገዥዎች  እየተነዱ   በማያውቁት ኣጀንዳ  ገብተው እርስበእርሳቸው ይፋጃሉ ።

ይህ ፍጅት ሊጠፋ ከሆነ  በኢህኣደግ  እጅ ነው።

ያለው  ። ይህም  ባለፉት ሳምንታት በዜጎች ተጽኖ  ከተወዳዳሪ  ፓለቲካ ፓርቲዎችና ከህዝብ ጋር ያለኝን ችግር ለመፍታት ሀገራዊ እርቅና መግባባት ኣደርጋለሁ ፣ ሁሉም ፓለቲካዊ እስሮኞች እፈታለሁ፣ሙሱናና ኪራይሰብሳቢ ኣካላት ኣስወግዳለሁ  ብሎ የተናገረው ፣ ነገሮችን ብቻው  ቤት ዘግቶ  ተሰብስቦ ሊፈታቸው ስለማይችል  የተቀጣጠለውና  እየተቀጣጠለው ያለው  የተቃውሞ  የእሳት ሰደድ  አገር ከማጥፋቱ በፊት   እነዛ ኣደርጋቸው ኣለሁ ብሎ ቃል የገባቸው በፍጥነት ሊተገብራቸው ከቻለ ብቻ  ነው ። ካለበለዚያ  ሁኔታው እየተበላሼ ነው ። ይህ ካልሆነ ኣሁን ያለው እጅጉን ኣሸጋሪ ሁኔታ  እስከሀገርን የመበታተን ኣደጋ  ሊሄድ ይችላል ።

በሀገራችን ያለችሁ ያገባናል የምትሉ  የፓለቲካ ሀይሎች ፣ሙሁራን ፣ተማሪዎች  ታዋቂ ግለሰዎች የሀገር  ሽማግሌዎች  የሀይማኖት መሪዎች ፣  ቡዙሀን ( ስቢክ ማህበራት  )ኣገር ሳይኖር በዝህች ለምለም ኣገራች ኖሮን ማንም ሰላማዊ ንሮ መስርተን ልንኖር ኣንችልም በመሆኑ  በኣሁኑ ጊዜ ኣንገታችን ደፍተን ዝም የምንለበት እና የምንተኛበት ወቅት ኣደለም ። ስለዚህ ኣሁን ያለው ቢሄር ቶኮር የማጋጨት   ዘመቻ  ቆሞ  ዝም ብሎ  መመልከት የለበትም ። ኣሁን በኢህኣደግ ይደረግ ያለው መሰረታዊ ለውጥ የማያመጣ እንደ ዘይት  ወይ እንደ  እንሳስላ ተቀባብቶ  እየሄደ ያለው ታሀድሶ እጃችሁ ታገቡ ዘንድ  ሀገራችን ለመዳን ልትረባረቡ  የኣክብሮት ጥሪዬን ኣቀርባለሁ ።

እናንተ ሀገራችሁ በተባላሸ ሰርኣት ምክንያት በዘርፈ ቡዙ ሽግሮች ምክንያት ጥያቄ ያላቹ ወጣቶች ፍትሀዊ ለውጥ ሊመጣ ከሆነ መጀመሪያ የተረጋጋች ሀገር ልትኖሮን  ይገባል በመሆኑም በቢሄር በዘር ልዩነት በስሜት እየተነዳቹ  ህዝባችሁ በመግደል የሀገራቹሁና  የህዝባችሁ ሀብት   ኣውድማችሁ ሀገር የለላችሁ ከምትቀሩ ማንነታቸው የማይታወቅ ባገር ውስጥና በውጭ ተደብቀው በማህበራዊ ሚዲያዎች እና በሌሎች በሚያሳራጩት ሀላፍነት የጎደላቸው ሴሮኞች እየተነዳችሁ ሀገራችሁና ህዝባችሁ  ከመግደል ከማማውደም   ኣቁማችሁ ረጋ በማለት ቆም ብላች በማሰብ ነገሮች ወደ ሰላማዊ ቦታቸው ትመልሱዋቸው ዘንዳየሰላም ጥሬን ኣቀርባለሁ። በተለይ ደግሞ ቢሄር ተኮር  ኦሮሞ ሱሟል ፣ትግራይ ኣማራ ወዘተ በማለት  ወንድም ለወንድም መናቆሩ መቋጫ ያገኝ ዘንድ የወጣት ግዴታችሁ እንድትወጡ በማክበር ጥሬን ኣቀርባለሁ ።

በሁሉም ስርኣቶች ፍትህ ኣጥታችሁ ወደ ውጭ የተሰደዳቹ ኢትዮጱያውያን ሁሉ በሀገራቹ ያለ ችግር በውስጥ ካለን ወገኖቻችሁ እኩል የችግሩ ተቋዳሽ ናችሁ በመሆኑም ያላችሁን የሰለጠነ የኣለም እውቀትና  ተሞኩሮ በመሰነቅ በሀገራችሁ እየታዬ ያለው መከራ የችግሩ ፈች ኣካል ሁናችሁ ትገኙልን ዘንድ የከበረ ሰላማዊ ጥሬን ኣቀርባለሁ።

የሀገራችን ጸጥታታ ሃይሎች ሆይ በኣሁኑ ጊዜ የገዥ ፓርት መሪዎች በፈጠሩት እጅጉን ዘርፈ በዙ ሽግሮች  የራበው ፣ስራ ያጣ  ፣ፍትህ የተነፈገው ኣብዛኛው የተማረ ወጣት ዜጋ፡ በሀገሩ ለመኖር ተስኖት  በማወቅ ይሁን ባለማወቅ በትንሽ ምክንያት ተነሳስቶ  በመላው  ሀገሪቱ  ሂወትና ሀብት ሲያጠፋ ይታያል ።ጸጥታ ሀይሎችም ኣደጋው ለመከላከል  በተሰጣችሁ ትዛዝ መሰረት  ለመከላከል በማለት በዜጎች ላይ ብዙ ሂወት የመጥፋትና  ( መግደል ) ኣካል መጉደል ታይቱዋል  ።ባለፉት ሁለት ኣመታት ደግሞ በሽ የሚቆጠሩ ዜጎች ሂወታቸው በጥይት ኣልፏል ።በመሆኑ የጸጥታ ሀይሎች የምታደርጉት ጸጥታ ለማስከበር ተብሎ የመትፈጽሙት ግድያ ሂወት እንደመጠበቅ ፈንታ ንብረትን ለመከላከል  ወይ ለመጠበቅ ቅድሚያ ሰጥታችሁ ለወጣቶች ሞት ግን ከንብረት በታች በማየታችሁ ለራሳችሁ ቡዙ ሂወት ከፍላችሁ   ቡዙ ዜጎች ኣጥፍቷችኃል ።በመሆኑ በእኔ እምነት  ከሆነ የወደመ ሀብት መውደም ኣልነበረበትም ።ምንም እንኳን በህገወጥ የተሰበሰበ ሀብት ቢሆን ከመቃጠል ይልቅ ለወደፊት ምንጩ ተጣርቶ በሀገር ጥቅም ቢውል ኣከፋም ነበር ።ግንደግሞ ወድሟል በቃ ኣይመለስም ። ያፈራው ሰው ነው ግንደግሞ ሀብት ሊተካ ይችላል ።ሰው ግን ኣይተካም ።ስለዚህ ለዜጎች በጥይት  ከማጥፋት ወንጀል ለፈጸሙ ወደ ፍርድ  ማቅረብ ተገቢ ነበር ። በመሆኑ በዜጎቻችሁ ግድያ መፈጸም ኣልነበራችሁም  ።ለወደፊትም በዜጎቻችሁ ከጭካኔና  ከግድያ ብትቆጠቡ የተሻለ ነው ሂወት ክቡር ነውና ። እርግጥ በራሳችን ላይ ግድያ እየተፈጸመብን እንዴት  ዝም  እንላለን
ትሉ ይሆናል ለህዝብ የቆምኩ ነኝ የሚል ጸጥታ ሀይል  በሲቢል ያልታጠቀ ህዝብ ሲመታ በትእግስት መከላከል ኣለበት እላለሁ ።

በሀገር ውስጥና በውጭ የምትገኙ ሀቀኛ ምዲያዎች ከዘረኝት ቢሄር ተኮር በስሜት ከመቀስቀስ በመራቅ በሀገራችን ተከስቶ ላለው ቢሄር ተኮር ግጭት ሁሉም ያገባናል የሚሉ ወገኖች በእኩል በተለይ ደግሞ ነፍጥ የታጠበቀው የኢህኣደግ ቡዱን  የሽግሩ ፈች ሁነው ይገኙ ዘንድ ሰላማዊ  ሰላማዊ ምክር ትሰጡት ዘንድ ጥሬን  ኣቀርባለሁ ።
እናንተ  በኣገር ወዳድነት   ሽፋን በማድረግ ፣ በፌስቡክ በሬድዮ ፣በተለብዥን ፣በእንተርነት ሀገርና ህዝቦቻ ለመበታተን ተደብቃችሁ ዘር ተኮር መርዛችሁ በመርጨት በተለይ ደግሞ ከ7 ሚሊዮን በላይ ህዝብ እና የኢትየጱያ ሀገራችን እንደሌሎች ህዝቦች መሰረታዊ እሴት የሆነ የትግራይ ህዝብ ከክፉ የኢህኣድግ ሰርኣትና መሪዎቹ  በኣገር ኣቀፍ ደረጃ  ተዘርገተው  ከኢህኣደግ መሪዎችና ኣጋሮቻቸው ኣመራር  ተሻርከው ኣገር እያጠፉ ያሉ ሙሶኞች የኣንድ ሳንቲም  ሁለት ገጽታ ናቸው በማለት  በጠላትነት መፈረጅ  ብታቁሙ የተሻለ ነው ።

የትግራይ ህዝብ እኮ በሁሉም የሀገራችን ክልሎች የተሳማራው ኣገር ለመውረር ሳይሆን ከጥንት ጀምሮ  ሁሉም የሀገራችን ክልሎች ሀገሬ ነው በማለት ይኖር ስለነበረ ፣ የሌሎች ክልሎች ህዝቦችም ልክ እንደ የትግራይ ህዝብ  የኢህኣደግ ገናጣይ በቋንቋና በባህል ፈደራሊዝም  ኣጥር ሰብረው  በፈለጉት ክልል  ሰርተው ፣ንሮ መስርተው ፣ወልደው ተጋብተው ይኖራሉ  ።የትግራይ ህዝብም ከነዚህ የተለዬ ኣይደለም ። ከገዥ ፓርት ባለስልጣና በመሻረክ የህዝብ ሀብት የሚመዘብሩም ከሁሉ ቤሄሮች የሚገኙ ግለሰዎች ሌበች ኣሉ ። ሁሉም ህዝቦች የኣማራ የትግራይ ፣የኦሮሞ  የጋንቤላ ፣የኣፋር የሱማል ፣የደቡብ ህዝቦች ህዝብ ግን እኩል ተጎጂ ነው ።  ኣሁንም የኢህኣደግ ኣማራር ለከፋፍለህ ስርኣቱ  ለማሳካት  በቋንቋና በባህል የተከለለ ፈደራሊዝም በማድረጉ የማንም ቢሄር ዜጋ ከክልል ወደ ክልል ተንቀሳቅሶ   ንሮ መስርቶ የፈለገውን ሀብት ኣፍርቶ እዳይኖር ፣እንዳይ ሰራ  ፣በጋብቻ እንደድሮ ተሳስሮ ተፋቅሮ እዳይኖር በማድረጉ የተፈጠረ ነው  ። እንጅ ኣሁንም ኣገሬ ነው ብሎ በሚኖርበት ኣገር እየተገለለ መገደሉ ደክሞ ያፈራው ሀብት መውደሙና መዘረፉ ፍትሀዊ ኣደለም ።

በመላው ሀገራችን ከኢህኣደግ ባለስልጣናት ተሻርከው የሀገራችን ሀብት የመዘበሩ እና እየመዘበሩ ያሉ  ከኣመራም ፣ከትግራይም ፣ከኦሮሞም ፣ከደቡብም ከሌሎች ክልሎችም  መሪዎችን ተጠግተው ያለኣግባብ የበለጸጉ ፣ኑሮዋቸው የናጠጠ ኣሉ ። እነዚህ ሌቦች ከሁሉም ክልሎች ቢሄሮች የሚገኙ ጥቂት ናቸው ።እነዚ የትግራይ ህዝብ በባዶ ሆዱ ሰርቶ ደክሞ ያፈራው ሀብት እንዲወድም እንዲገደል የሚቀሰቅሱ  የኢትየጱያ ህዝቦች ጠላቶች እና የነ ግብጽና  የሸኣብያ   ቅጥሮኞች መልእክተኞች ናቸው ።
ስለዚህ የኢትየጱያ ህዝቦች በሙሉ  የትግራይህዝብ በጅምላ ጠላት እንደሆነ ኣድርገው የሚነግሩዋችሁ ኮኑኑዋቸው ።ከዝህች ኣገር ትግራይ ወይ ኦሮሞ ወይ ዓፋር ወይ የሆነ ክልል ከጎደለ  አንዲት ኢትዮጱያ  የምትባል ኣገር ኣትኖርም ።
ኢትየጱያ ሓገራችን ህዝቦቻ እና  አንድነቷን  ፍቅራን ጠብቆ ለዘልኣለም ያኑሩልን  ያኑርል ።
ወድቀት ለሴሮኞች !!!!!!
ከአስገደ ገብረስላሴ
መቀለ

Share
error0

Facebook Comments

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

The Latest Ethiopia News

To Top